Huluba – An Ethiopian Singer Digital Persona

Huluba - Ethiopian Singer Digital Persona
Huluba Going Global

Huluba going global!

I started this project with an ambition to elevate and promote the unique Ethiopian pentatonic melodies and musical instruments through modern music, a digital persona, and original lyrics. We are almost there, Huluba's music is hitting global streaming platforms this week!Including Spotify and Apple Music, her songs will be available on all major platforms.

The original lyrics are hit-level, and the new BandLab master sounds incredible. Click here to listen Huluba's songs on Spotify and Apple Music.

Spotify
iTunes
YouTube
Huluba - Ethiopian Singer Digital Persona

About Huluba (Short Bio)

Huluba - Ethiopian Singer Digital Persona

Huluba (ሁሉባንቺ) is an Ethiopian singer digital persona created by Gizaw Legesse to explore new possibilities in music, storytelling, and cultural expression through artificial intelligence. Imagined as a thoughtful Ethiopian woman in her mid-thirties, Huluba is recognised by her distinctive dreadlocks, soulful voice, and emotionally expressive performances.

 

Huluba performs original songs in both Amharic and English, all written by Gizaw Legesse. Her music blends Ethiopian folk traditions with contemporary influences including roots reggae, blues, jazz, and world music, while remaining deeply rooted in Ethiopian pentatonic melodies and traditional instruments such as the washint, masinqo, and kebero.

 

More than a virtual artist, Huluba is an ongoing creative project that celebrates Ethiopian language, poetry, and musical heritage through original compositions, bringing timeless stories and new musical ideas to audiences in Ethiopia and around the world.

Listen her music below.

Yabseleslewal - ያብሰለስለዋል

LYRICS BY GIZAW LEGESSE

[Chorus]

በልቡ እያወቀ ሰውነት ላይሆነው

አላምጦ እያኘከ ነገር ይበላል ሰው

እንዲህ ያደርገዋል ሰው ፍቅር ሲጠማ

ያብሰለስለዋል እድሉን ሲቀማ።

[Verse 1]

እንዳይብስ ለከርሞ የዘንድሮ ጣጣ

ተመስገን እያለ የባሰ እንዳይመጣ

እጥፍ ተበድሎ እጥፉን ሲቀጣ

ስንቱ መና ቀረ ላቡ ዋጋ እያጣ

እንዲያው ለመሆኑ...

ተሳድቦ ላገኘ አመስግኖ ላጣ

ባንድ ይለቀስ ይሆን? አይቀር ሞት ሲመጣ

[Post-Verse - Male vocals rap]

በክረምቱ ከደመነ ቢዘገይም ለሚዘንበው፤

ከሚሆነው በኋላ እንጂ ስለሆነው አታስበው፤

የጨለመው ለሚነጋ የመጣውም ለሚሄደው፤

ከሚሆነው በኋላ እንጂ ስለሆነው አታስቢው።

[Chorus]

...

[Verse 2]

ሀቀኛ ሲከስር ማስመሰል ሲያዋጣ

ውሸት አስከብሮ መጠየቅ ሲያስቀጣ

ማተቤን እያለ መአት እንዳይመጣ

ለእውነት በመቆሙ የላቡንም አጣ።

እንዲያው ለመሆኑ...

ተሳድቦ ላገኘ አመስግኖ ላጣ

ባንድ ይለቀስ ይሆን? አይቀር ሞት ሲመጣ

[Post-Verse - Male vocals rap]

...

[Outro | chorus refrain]

...

ያብከነክነዋል

እድሉን ሲቀማ።


Qinee - ቅኔ

LYRICS BY GIZAW LEGESSE

[Verse 1]
የኔና አንተ ጊዜ

እየተቃቀፉ እንደ መገፋፋት

ባይን እየተያዩ እንደ መተጣጣት

ሳይመሽ እየተኙ ሳይነጋ እንደመንቃት።

ምን ሆነ መሰለህ በዚያ በቀናችን

አበሩ እንደፀሐይ እንዳላስባለችን

ጀምበሯም እንደሰው አሽሟጥጣ ከዳችን።

[Chorus]

የኔና አንተ ነገር የኔና አንተ ቅኔ

ተንሳፎ መቅረት ነው ልክ እንደ መንጽሔ

ለጽድቅ አያበቃ አይሰጥ ለኩነኔ።

[Verse 2]

የኔና አንተ ቦታ
ላይገናኙበት የሚቃጠሩበት

እየተገኙበት እንደማይኖሩበት

ሙጃ እንደወረሰው የባለፀጋ ቤት።

ምን ሆነ መሰለህ የጋራ ቤታችን

ተገንብቶ ሳለ በሳቅ በቡረቃ

ተሰነጣጠቀ በኔም ባንተም ሲቃ።

[Chorus]

...

[Bridge]

ጨርሰህ ላትቆርጥ፣ ላያስችለኝ እኔ

እየተነፋፈቅን እያለሁ ከጎንህ፣ እያለህ ከጎኔ

ይኸው ነው የኔ ዓለም

የኔና አንተ ነገር፣ የኔና አንተ ቅኔ።

[Chorus]

...

MITHAT ALAT - ምትሃት አላት

LYRICS BY GIZAW LEGESSE

[Chorus]

እየዘነበ ነው፣ እምባ በፊትዋ ላይ

የሷ ይሁን የማ፣ በግልፅም አይታይ

ሆዷ እየጮኸ እያሳበቀባት

ጦሟን እንዳደረች እየነገረባት

ያልተበላበትን ሰሀን አጠበላት!

[Verse 1]

ወላድም አይደለች ድንግል ናት እያሏት

መካንም አይደለች የሚሊዮን እናት

የሚመፃደቁ የሚታበዩባት ብዙ ልጆች አልዋት።

.

ሀገርም እንደሰው ሚስጥር ከከበባት

ማስመሰል መሸንገል እንዲህ ሲዋጣላት

የወደቀች እንደሁ ማነው የሚያነሳት?

[Chorus]

...

[Verse 2]

በእነ እማማ ጊዜ  ከደመነ ይዘንባል

በእነ አባባ ጊዜ ከወገገ ይነጋል

በኛ ጊዜ ደሞ እየሆነ ሳይሆን እያልሆነ ሆኗል።

.

ሀገርም እንደሰው ቀን ሲጨልምባት

ሽፍታ በትር ይዞ ሰላም ሲሰብ-ክባት

አርበኛ ነኝ ያለው እንዴት አርጎ ሸጣት?

[Bridge]

ትነሳ ይሆናል ቀኑ ሲወጣላት

ትገለጥ ይሆናል ጊዜው ሲደርስላት

ሀገሬ እንደሆነች አንዳች ምታት አላት!

ኢትዮጵያ እንደሆነች አንዳች ምታት አላት!

[Chorus]

...

 

Hope Never Fades - በፍቅር ያመኑ

LYRICS BY GIZAW LEGESSE

[Intro]

Hope never fades. . .

[Verse 1]

ዓለም አቀበት ነው አባጣ ጎርባጣ

ህይወት ፈተና ነው እርካታ ሚያሳጣ

ሌሊቱ ሲረዝም መከራ ቅጥ ሲያጣ

የማያልፍ ይመስላል ፀሐይ የማትወጣ።

[Chorus]

ሆኖም ...

በፍቅር ያመኑ ብዙ ሰዎች አሉ

በሐምሌ ደመና ሰማይ ያፈካሉ

በሚያኮማትር ውርጭ ሙቀት ያፈልቃሉ

በመከራ ዝናብ ያዘን ማቅ አስጥለው ያስወረውራሉ።

እንዲህ ያሉ ነፍሶች - ሀገር ያቀናሉ

ለራደ ቤተሰብ - ማገር ይሆናሉ

ለሰለለ እስትንፋስ - ህይወት ይዘራሉ

የሞተ ያለቀ - የደረቀ ተስፋን - ያለመልማሉ።

[Post-Chorus]

People make life meaningful,

Every moment beautiful.

Souls that shine the light across,

Because of them, hope never fades

Hope never fades.

[Verse 2]

ደግሞ አንዳንድ ሰው ቀድሞ ይሸነፋል

የፍቅር ሸማውን ባንዴ አውልቆ ይጥላል

አብሮ መብላት ጠልቶ ብቻውን ይሻማል

ሌሊቱ ቢረዝም ያኛውም ቀን ያልፋል።

[Chorus]

...

[Post-Chorus]

...

[Outro]

በፍቅር ያመኑ ብዙ ሰዎች አሉ

ለሰለለ እስትንፋስ ህይወት ይዘራሉ

የሞተ ያለቀ - የደረቀ ተስፋን - ያለመልማሉ።

Iski Nigerugn - እስኪ ንገሩኝ

LYRICS BY GIZAW LEGESSE

[Intro]

በደመናማ ቀን ፀሐይ ባጣ ሰማይ

የተፈጀን ጊዜ ጥላ እንደማያሳይ

ጠንቅቄ እያወኩኝ

ሰው ስጠይቅ ዋልኩኝ

[Chorus]

እስኪ ንገሩኝ ሰዓቱን

እስኪ ንገሩኝ ጊዜያቱን

እየነጋ እንደሆን ወይ ቀድሞ መምሸቱን

እየነጋ እንደሆን ወይ ቀድሞ መምሸቱን

[Verse 1]

ለሰው ባትታየው

እድል እጣ-ፈንታው ከግዝፈት ረቅቃ፤

ከእቅፉ ያገኛታል

ከልቡ ከሻተ ከእንቅልፉ ከነቃ።

ባንተ ልዕልና

በብርሃን በትር ነፍሱን ያነገሰ፤

ጊዜ አያባክንም

ይኖረዋል ደግሞ እየመላለሰ።

[Chorus]

[Verse 2]

እየደባበሰ

ከህልም ዓለም ነጥቆ ቀስቅሶ ሲያነቃኝ፤

የክት ጉዳዬ

እንደዘበት ፈልቆ እንደፀሐይ ሞቀኝ።

ባንተ ፀሐይነት

ሸማውን አውልቆ ፀጋን የለበሰ፤

ቦታ አይወስነውም

ይቀኘዋል ስምክን ህዋ እየነቀሰ።

[Bridge]

ከጥንት ጀምሮ

ፍቅርን ለመተርጎም

ሰው መላ ሲመታ፤

እኔ ዛሬ ገባኝ

እንደማይወሰን

በጊዜና ቦታ።

[Chorus]

Scroll to Top